የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/Women-Leage-leader.jpg

የሴቶች ሊግ መሪየሺ ወልዴ

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የብልጽግና ፓርቲ ክንፍ በመሆን የከተማዉ ሴቶች የወቅቱን መድረክና ተልእኮ ተገንዝበዉ በብቃት የመፈጸም ፤ ህብረተሰባዊ ለዉጥን የማፋጠን ፤የከተማችን ሴቶች በጋራ አላማቸዉ ዙሪያ የማሰለፍና የትግል መድረክ በመሆን ጥቅሞችን የማጣጣም ቁልፍና ወሳኝ ተልኮ ይዞ የተቋቋመ የሴቶች የፖለቲካ አደረጃጀት ነዉ፡፡

ሊጉ ሴቶች በከተማችን በሚካሄደዉ ልማት ንቁ ተሳታፊና ከሚገኘዉም የኢኮኖሚ እድገት ተጠቃሚ መሆናቸዉን ማረጋገጥ የሴቶችን ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲሁም ሴቶችን ዝቅ አድርገዉ የሚመለከቱ አስተሳሰቦችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና ሴቶች የራሳቸዉን የዝቅተኝነትና የበታችነት አመለካከት ማስወገድ፤ በየደረጃዉ እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና የዉሳኔ ሰጭነት ስልጣን እንዲኖራቸዉ በዲሞክራሲያዊ ስርአት በህገመንግስቱ እንዲሁም በሀገራዊ ምክክር መድረክ ዘላቂ ተሳትፎና አስተዋጽኦ በማድረግ የተጀመረዉን የብልጽግና ጉዞ በማፋጠን ተጠቃሚነታቸዉን ማረጋገጥና የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን መጻኢ ግዜ ብሩህ ማደረግ ይጠበቃል፡፡

የእኛ ክስተቶች

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300647
Total Visitors