ማኒፌስቶ

የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ

እኛ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የሀገራችን ኢትዮጵያን ዕድገትና የጋራ ብልጽግና እውን ለማድረግ በመነሣት፣ ሀገራችንን ወደሚቀጥለው ምእራፍ ለማሻገር አዲስ ራእይና አዲስ ትርክት እንደሚያስፈልግ በማመን፣ የሕግ የበላይነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት፤ የግለሰብና የቡድን መብቶች በሚዛኑ የሚከበሩባት፤ ዜጎች ከድህነት ተላቀው በብልጽግና የሚኖሩባት፤ ጠንካራና ቀጣይ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚታይባት፤ በአህጉራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊው መድረክ ላይ ጉልህ ሚና የምትጫወት ኢትዮጵያን ለማየት ባለን ተስፋ፣ የበለጸገች፣ ኅብረብሔራዊ ማንነቷ የዳበረና አንድነቷ የተጠናከረ ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ባለን ቁርጠኝነት፣
ይህንንም ለመተግበር በመደመር አስተሳሰብና በአንድነት ቅኝት በመነሣት፣ ልናያት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመገንባት የእያንዳንዳችንን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት፣ የበኩላችንን ሚና ለመጫወት በከፍተኛ ቆራጥነት ተሰባስበን መታገል በማስፈለጉ፣ የብልጽግና ፓርቲ (ብልጽግና) የሚመራበት የመተዳደሪያ ደንብ መቅረጽ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ ይህ መተዳደሪያ ደንብ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተደነገጉትን ሕጎች የሚያከብር የብልጽግና ፓርቲ (ብልጽግና) ሰነድን በመጀመሪያው ጉባኤያችን መክረንበት ሕጋዊ የፓርቲውን ሰነድ አድርገን አጽድቀናል።

የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ መስኮች በርካታ አዎንታዊ ለውጦችን አስመዝግባለች። እነዚህን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች አስጠብቆ ለማስፋት፣ ስሕተቶችን ለማረም እንዲሁም የዛሬውንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ወቅቱ ለሚጠይቀው ትግል በሚመጥን መልኩ ለመደራጀት አምነው የፈጸሙትን ውሕደት መነሻ በማድረግ ይህ የ”ብልጽግና ፓርቲ” ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300550
Total Visitors