አቶ ሞገስ ባልቻ

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ መልዕክት

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ የማንነት፣ የእምነት፣ የባህል፣ የቋንቋና የፖለቲካ አስተሳሰቦችን በህብር ያቀፈች የብዝሃነት መገለጫና ተምሳሌት ሀገር ነች። ዜጎቿ በብዝሃነት መገለጫዎች ቢለያዩም በመከባበርና በመቻቻል ልዩነታቸውን ውበታቸው አድርገው ለዘመናት ኖረዋል። የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት በመስዋዕትነት ጠብቀው ለእኛ አስተላልፈዋል።

ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ወዲህ የተፈጠሩ የተዛቡ ትርክቶችና የፖለቲካ እይታዎች ግን እነዚህን አያት ቅድመ አያቶቻችን እንደ ጸጋ ተቀብለው ሀገር ያፀኑባቸውን የወል እውነታዎች እንዲሸረሸሩ፣ ብሎም የጥንካሬያችን ሳይሆን የመዳከማችን ምንጭ እንዲሆኑ አድርገው ቃኝተዋቸዋል። በየዘመኑ ብቅ ያሉ መንግስታትና የፖለቲካ ሃይሎች አንዳንዶቹ በእሳት ላይ ቤንዚን እንዲሉ መከራችንን ሲያራዝሙብን፤ ሌሎቹ ባልተሟላና በተንሸዋረረ የመፍትሄ እርምጃ ችግሩን ይብስ ሲያወሳስቡት ቆይተዋል።

ሀገራዊ ለውጡ የወለደው ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችን የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ስብራቶች በዘላቂነት የሚፈቱት ሁሉን አቀፍና ዴሞክራሲያዊ በሆነ፣ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን በሚያፀና እና በወንድማማችነት/ እህትማማችነት ማዕቀፍ ውስጥ በሚያይ መፍትሄ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። በመሆኑም ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በህግ፣ በአሰራርና በተቋም ደረጃ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ እንዲወጣ አድርጓል። within the framework of brotherhood/sisterhood. Therefore, our national unity has become the main agenda at the level of law, procedure and institution.

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤትም በዚሁ እሳቤ ከከተማችን ነዋሪዎች በምርጫ የተሰጠውን ሃላፊነት በላቀ የሃላፊነት መንፈስ ለመወጣት እየተረባረበ ይገኛል። ባለፉት አምስት አመታት የትልቋ ኢትዮጵያ ማሳያ በሆነችው አዲስ አበባችን የኢትዮጵያ ብልፅግና አይቀሬ መሆኑን ያረጋገጡ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ድሎችን አስመዝግበናል። ግዙፍ የብልፅግና አሻራዎች በከተማችን ተተክለዋል።

በጉዟችን መሃል ሰው ሰራሽ እና መዋቅር ወለድ ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም ፈተናዎችን ወደ እድል እየቀየርን አቅማችንን በውጤት፣ ፈተናን በስኬት እየቀየርን በአብሮነትና ወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ጉዟችንን ቀጥለናል። አሁንም በየደረጃው ያለው የፓርቲያችን አመራር፣ አባል እና ደጋፊው ህዝብ አብሮነታችንን በማፅናት ፈተና የሆኑብንን ፅንፈኝነት/አክራሪነት፣ ውጤት አልባነት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በፅናት በመታገል አይቀሬ የሆነው ሁለንተናዊ ብልፅግን እውን እናደርጋለን።

በዚህ ሂደት መላው የከተማችን ነዋሪ እንደ ሁል ጊዜው ከጎናችን ሆኖ ያልተቆጠበ ድጋፉ እንዲቸረን፤ እንዲሁም ዲሞክራሲን በማፅናት የማይተካ ሚና ያላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ሁሉም የዴሞክራሲ ተቋማት ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ብልፅግና አብረውን እንዲሰሩ ጥሪያችንን አቀርባለሁ።

አመሰግናለሁ!!

Majored in Political Science

Law School and Civil Rights Attorney

Director of the Developing Communities

Deputy Attorney General Media Project

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300469
Total Visitors