አበባ ከተማ አስተዳደር የሕንጻዎችን ቀለም በተመለከተ ማብራሪያ ሰጠ

ሰኔ 14, 2022

አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እንድትሆን እና ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚመጥን ገፅታ እንዲኖራት ከሚሠሩ ሥራዎች አንዱ የሕንጻዎችን ቀለምና ቁመት የሚወስን አሠራርን መተግባር መሆኑን አስታውቋል።በእስካሁኑ ሂደት የከተማዋ ሕንጻዎች ያለምንም ቁጥጥርና ወጥነት በጎደለው መንገድ የሚቀቡ ቀለማት የከተማዋን መልክ ቡራቡሬና ዥንጉርጉር ከማድረጋቸውም በላይ÷ የሚገነቡ ሕንጻዎች ዲዛይን በዘፈቀደ መሠራቱ የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ ጎድቶታልም ነው ያለው አስተዳደሩ፡፡ስለሆነም ይህን ችግር መልክ ለማስያዝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከብዙ ዓለም አቀፍና አፍሪካዊ ከተሞች ተሞክሮ በመውሰድ÷ ለከተማዋ የሚስማማ የሕንጻ ቀለማት ደረጃን አጥንቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡በመሆኑም በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳተፉበት ሁኔታ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ለከተማዋ የሚስማሙ 13 ዓይነት ቀለማት መለየታቸውን ገልጿል።በዚህ መሰረት በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ለከተማዋ በመለያነት ከተመረጡ ቀለማት መካከል የሕንጻ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን÷ ይህ አሠራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክፍለ ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ መገባቱንም ነው ያስታወቀው፡፡

 

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300583
Total Visitors