ሁለተኛው ዙር የአመራር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ

ሰኔ 13, 2022
3
4
"አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ - አዲስ ሀገራዊ እምርታ!" በሚል በአዲስ አበባ ከተማ ላሉ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሁለተኛው ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል። የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ስልጠናው ለአመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፍጠር ወንድማማችነት እና እህትማማችነት በማጎልበት የፓርቲውን ዓላማ እና እሳቤ ያነገበ፤ ለተግባራዊነቱም ብቁ አመራር መፍጠር ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም አመራሩ አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ እና ሀገራዊ እምርታ በማንገብ ወደ ብልፅግና መጓዝ የሚችልበት አቅም የሚፈጥር ስልጠና መሆኑን አቶ መለሰ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን በዚህ በሁለተኛው ዙር ስልጠና የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል። በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመረቀ። አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ የሚገኝው የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ ብቁ የጤና ተቋማት በመገንባት ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎትን ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው በአሁን ሰአት ለምርቃት የበቃው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300567
Total Visitors