ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ሰኔ 13, 2022
5

ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ ፤ ተዘዋውረው የጎበኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ጊዜ በፍጥነት እንዲሁም ጥራታቸውን ጠብቀው ስለሚጠናቀቁበት ሁኔታ ከየፕሮጀክቶቹ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተነጋግረዋል፡፡ ተዘዋውረው ከተመለከቷቸው ፕሮጀክት መሃከል የአፍሪካ ኢኖቬሽን ማእከል፤ የአዲስ አበባ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ፤ የታላቁ የቅርስና የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክትና የካ ቁጥር ሁለት መኪና ማቆምያ ይገኙበታል፡፡ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጄክቶቹ የገጠማቸውን የሲሚንቶና የውጪ ምንዛሬ እጥረት በመቅረፍ ጥራታቸውን ጠብቀው በብቃት የመጨረስ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300460
Total Visitors