የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።

ሰኔ 13, 2022
2
1
ላለፉት ስድስት ቀናት "አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ - አዲስ ሀገራዊ እምርታ" በሚል ለከተማዋ ከፍተኛ አመራር ሲሰጥ የነበረው የስልጠና መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በማጠቃለያ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሀገራዊ የለውጡ ሂደት ፈታኝ ቢሆንም ይሄንን ፈተና ለማለፍ በጥበብ እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የአመራር ዘይቤ በመከተል ዛሬ ላይ መድረስ መቻሉን ከዚህ ስልጠና አመራሩ ግንዛቤ ማግኘቱን ተናግረዋል። በለውጡ ሂደት ተስፋን የሚጭሩ ትላልቅ ስራዎች መሰራታቸው በተለይም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የደህንነት፣ የሰላምና የጸጥታ ተቋሞቻችን ላይ የተደረጉ መሰረታዊ ሪፎርሞች በጊዜያዊነት ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ ግንባታው ወሳኝ የሆነ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል የተሰራውን ስራ ሰልጣኙ በተግባር ጭምር እየተመለከተ የሰለጠነበት ሁኔታ እንደነበር አንስተዋል። አጠቃላይ ስልጠናው በአመራር የመሪነት ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተቋም ግንባታ፣ ተቋማዊ አሰራሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውና ሀገራዊ ለውጡ ተቋማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ሁሉም ተባብሮ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል። የፓርቲ ተቋማዊ ግንባታ ለመንግስትና ለሀገራዊ ጥንካሬ ወሳኝ ነው፤ ጠንካራ መንግስት የሚኖረን እና ጠንካራ ሀገር የምንገነባው በጠንካራ ፓርቲ ነውና አመራሩ ተግባራትን አቀናጅቶ መምራት እንደሚገባውም ከንቲባዋ አሳስበዋል።
https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

አግኙን
0116674406
P.O.Box: 1352
300429
Total Visitors