Other news

July 23, 2023

1፣ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ እና ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ በሌማት ትሩፋት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ። በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ በየካ፣በቂርቆስና በለሚኩራ ክፍለ ከተሞች የተሰሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን የተጎበኙ ሲሆን በጓሮ አትክልት፣ በንብ ማነብ፣ በዶሮ እርባታ እና በከበት ማደለብ እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተው በጎ እምርታ ያስመዘገቡ መንደሮችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ጉብኝት በተከናወነባቸው ክፍለ ከተሞች አነስተኛ ቦታን በመጠቀም የተሰሩ ስራዎች ከሌማት ትሩፋት በላይ የከተማ ግብርና እንቅስቃሴን ለማሳደግ የሚያስችል ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ማከናወናቸውን ለመገንዘብ ተችሏል። ከሁሉም የሀገራችን ክልሎች የተወጣጡ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በጉብኝቱ ወቅት በርካታ ልምዶችን መቅሰማቸውን ገልፀው በቀጣይ በከተሞቻቸው ውስጥ መሰል ተግባራትን በተሞክሮ መልክ ለማስፋት ጠንካራ ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

2የስራዎቻችን ሁሉ ማጠንጠኛ የብልፅግና እሳቤ የዜጎችን ህይወት እንዲለውጥና እንዲያበለፅግ ማድረግ ነው!!”

አቶ ሞገስ ባልቻ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የተቋሙ /ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይመር ከበደ እና የየክፍለ ከተማው የፓርቲ /ቤት ኃላፊዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ /ቤት በመገኘት የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፤ ሁሉም ክፍለ ከተማ ባለበት እንዲህ አይነት መሰል ጉብኝቶች ማከናወን አመራሩ ሁሉንም የከተማችን መዋቅሮችና ነዋሪዎች በቅርበት እንዲያውቃቸውና እንዲደግፋቸው እንደሚያስችል ገልፀዋል።

የስራዎቻችን ሁሉ ማጠንጠኛ የብልፅግና ፓርቲ አስተሳሰብ የሁሉንም ዜጎች ህይወት እንዲለውጥና እንዲያበለፅግ ማድረግ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የህዝባችንን አንገብጋቢ ጥያቄዎች በመመለስ ዘላቂ ልማትና አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ አመራሩና አባላት የተደራጀ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

በአቶ ሞገስ ባልቻ የተመራው የጉብኝት ቡድን ከክፍለ ከተማው ፓርቲ /ቤት በተጨማሪ የወረዳ 9 የብልፅግና ፓርቲ //ቤት የስራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን በአደረጃጀት፣ በተቋም ግንባታ፣ በአቅም ግንባታ፣ መረጃ

አያያዝን በማዘመንና በመሳሰሉት ጉዳዮች አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተመላክቷል።

የወረዳ ዘጠኝ የህዋስና የመሰረታዊ ፓርቲ አመራርና አባላትም አቅማቸውን በመገነባባት አቅመ ደካሞችን በመርዳት፣ ህገወጥ ተግባራትን በመታገልና በሌሎችም የልማትና የሰላም ስራዎች ግንባር ቀደም ሚናቸውን ለመወጣት እያደረጉት ያለውን ተሞክሮ አቅርበዋል።

3፣ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት በአዲስ አበባ የሌማት ቱሩፋትን እንቅስቃሴ በተመለከተ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ማድረግ ጀመሩ

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አመራርና አባላት በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘውን የሌማት ቱሩፋት የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ሴቶች ሊግ አስተባባሪነት የልምድ ልውውጥ እና የጉብኝት ፕሮግራም ማድረግ ጀምረዋል

በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በአንድ ማዕድ አሰባስቦ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ እየተጋ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በላቀ ትኩረት ለማረጋገጥ እንዲቻል የሴት ሊግ እና የወጣት ሊግ አደረጃጀቶች ድርብርብ ሀላፊነቶችን ወስደው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋገጥ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ አመራሩ፣ አባላት እና ህዝባችን እየተረባረቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ሀላፊው በጠ/ / ዐብይ አህመድ የተጀመረውንና ሁሉም ዜጋ የተመጣጠነ ምግብ እንዲኖረው የሚያደርገውን የሌማት ቱሩፋት እና የከተማ ግብርና ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግ የከተማችን ሴቶች በግንባር ቀደምነት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለልምድ ልውውጥ የመጡትን የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አመራርና አባላት የሁላችንም ከተማ ከሆነችው አዲስ አበባ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ልምድ ከመቅሰም በተጨማሪ ተሞክሯቸውንም በማካፈል ለጋራ ብልፅግናችን የጀመሩትን እርብርብ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ሞገስ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት የሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት / የሺ ወልዴ በበኩላቸው በጠ/ / ዐብይ የተጀመረው የሌማት ቱሩፋት ፕሮግራም ከንቅናቄ ስራዎች ተሻግሮ በሁሉም /ከተሞችና ወረዳወች በመደበኛነት እየተከናወነ መሆኑንና የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት እየደጎመ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዶሮ እርባታ፣ በንብ ማነብ፣ በከብት ማድለብ፣ በወተት፣ በእንቁላል እና በመሳሰሉት የሌማት ቱሩፋቶች እንዲሁም በጓሮ አትክልት እየተገኘ ያለው ስኬት በከተማችን አዲስ አበባ በውስን ቦታ ላይ ለመተግበር ያስቸግራል የሚለው የአይቻልም መንፈስ የተሰበረበት መሆኑን የጠቀሱት / የሺ ለልምድ ልውውጥ የመጡ የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አባላት በርካታ ተሞክሮዎችን እንደሚያገኙ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ እየተሳተፉ ያሉት የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት / ዘሀራ ሑመድ፣ የሊጉ /ፕሬዝዳንት ጠይባ ሀሰን እና አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የስራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት በተመረጡ /ከተሞች የመስክ ጉብኝት የሚያደርጉ ይሆናል።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
299119
Total Visitors