May 7

July 23, 2023

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት በየደረጃው ከሚገኙ የፓርቲ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር በመሆን የ2015 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ አከናወነ ።
የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፤ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም የጋራ ጥረት የተከናወኑ ስኬቶችን ለማጠናከር እና ቀሪ ተግባራትን ለመፈፀም በቀሪ ሁለት ወራት ዕቅዶችን በመከለስ ሁሉንም አቅሞች አስተባብሮ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የወጣቶችን፣ የሴቶችን እና የሌሎችንም የህብረተሰብ ክፍሎችን ጥያቄዎች በመመለስ ተጠቃሚነታቸውን የበለጠ ለማረጋገጥ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ያስረዱት ኃላፊው ለልማትና ለሰላም ቀናኢ የሆነውን ህዝባችንን የበለጠ በመቅረብና በማስተባበር ለላቀ ስኬት መትጋት ይገባል ብለዋል።
ቀጣይነት ያለው የአስተሳሰብ ግንባታ፣ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ሙሉ በሙሉ በዳታ ቤዝ ማስገባት፣ የህዋስ አደረጃጀቶችን ሞዴል ማድረግና ኮሮ አመራሮችን ማብዛት፣ የተጀመረውን የአመራር ምዘና ቀጣይነት ማድረግ፣ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን ህዝባችንን አሳትፎ መታገል፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን እንዲሁም አብሮነትን ማጎልበትና ለዚህ ተፃራሪ የሆነውን ፅንፈኝነትን በፅናት መታገል በቀጣይ ወራትም በትኩረት ከሚሰሩ የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች መካከል መሆናቸውን አቶ ሞገስ አስገንዝበዋል።
የከተማዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ባለፉት ወራት የአመራሩ አንድነት እየተጠናከረ መምጣት ለተመዘገቡ ስኬቶች ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከቱን በመግለጽ የህዝባችንን ጥያቄዎች ለመመለስ የበለጠ መጠናከር እና ክፍተቶችን መሙላት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ህብረ “ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊት ሀገር ናት፤ የብዙ ብሔሮች ቋንቋዎች ባህሎች የአለባበስ የአዘፋፈን ዘዬዎች ያሉባት ምድር ናት፤ እነዚህ ህዝቦች ተከባብረው፣ ተዋደው፣ ተደማምጠው፣ ተደምረው ከሰሩ የበለጸገች ሀገር ለልጆቻቸው መተው ይችላሉ።”
– የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

 

የበለጸገች እና “የበለጸገች እና ለሁሉም ምቹ የሆነች ሀገርን ለመገንባት ኢንዱስትሪዎቻችንን በማሳደግ፤ ዐቅምን በመፍጠር ፤ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ፈተናዎችን በማልፍ ኢትዮጵያን አንደኛዋ ትልቁ ኢኮኖሚ ማድረግ ይገባናል፤ አይሳነንምም።”
– ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300633
Total Visitors