May 6

July 23, 2023

በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ በሁሉም ክፍለ ከተሞች “ሴቶች ለብልፅግና፤ ብልፅግና ለሴቶች” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል
የከተማዋን ሀብቶችና ጸጋዎች አሟጦ በመጠቀም የሴቶችን ስራ አጥነት በመቀነስ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በአመራሩና በሴቶች ዘንድ መነቃቃትን ለመፍጠር ያለመው ይህ የውይይት መድረክ ሴቶች በአካባቢያቸው በሚካሄደው የሰላም፣ የልማት፣ እና የጸጥታ ተግባራት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ በንቃት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያስችላል።
በተጨማሪም በሀገራችን ብሎም በከተማችን የመጣው ለውጥ በሴቶች የለውጥ ፍላጎትና ጥያቄ ጭምር የመጣ በመሆኑ የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሀሳብ አስተያየቶችን እርስ በእርስ በመለዋወጥ የአንድነት አመለካከት በሴቶች ዘንድ እንዲጎለብት ያስችላል።
በደማቅ ሁኔታ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተከናወነ ባለው የሴቶች ውይይት መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ወደ ውይይት ከመግባታቸው አስቀድሞ ሀገራዊ የለውጥ ትሩፋት ለከተማችን ያስገኘውን ለውጦች የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

 

አገልጋይ መሪ የሆነ ከንቲባ አምስቱ ባህሪያት ፦
1ኛ. ማሰብ
2ኛ. ማድመጥ
3ኛ. ማሳመን
4ኛ. ማዘን
5ኛ. ማህበረሰብ መገንባት

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300508
Total Visitors