May 4

July 23, 2023

ፅንፈኝነት የተዛባ አስተሳሰብ እንጂ ብሔር የለውም !!”

አቶ አለማየሁ እጅጉ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴክተር ተቋማት የህዋስና የመሰረታዊ ፓርቲ አመራሮች የአስተሳሰብና የተግባር

አንድነትን የሚያጎለብት ስልጠና ተከናወነ

በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት /ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት የመሰረታዊ ፓርቲ እና የህዋስ አመራሮች በፓርቲው ፖሊሲዎችና አሰራሮች ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዘ ለሌሎች ከማስረፅ በተጨማሪ በተሰማሩባቸው ተቋማት ምሳሌ ሆነው አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመንና ፅንፈኝነትን፣ ሌብነትን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ታግሎ ማስተካከል እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

ፅንፈኝነት የተዛባ አስተሳሰብ እንጂ ብሔር የለውም ያሉት ኃላፊው ብሔርን የፅንፈኝነታቸውና የሌብነታቸው መደበቂያ በማድረግ መለያየትንና መጠራጠርን የሚሰብኩ አካላትን ሀገር አፍራሽ አስተሳሰብ በየደረጃው የሚገኘው አመራር፣ አባላትና ህዝባችን በፅናት ሊታገላቸው እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ / ሚኤሳ ኤለማ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነትን በተመለከተ በሰጡት ስልጠና እንደተናገሩት ብዝሃነታችን የሀይማኖት እና የብሔር ብቻ ሳይሆን የሀሳብም መሆኑን በመገንዘብ የውይይት ባህልን ማጎልበት እንደሚገባ አስረድተዋል

በአንድነትን ስም ለአንድ አይነትነት የሚንቀሳቀሰው የጠቅላይ አግላይነት ፅንፍ እና ራሱን የብሔር ጠበቃ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የተገንጣይ ብሔርተኝነት ፅንፉ የከፋ መዘዝ በሀገራችን በተግባር መታየቱን ያብራሩት / ሚኤሳ በሀገር አንድነትና በብሔር ማንነት መካከል ያለውን የህብረ ብሔራዊ አንድነትን ሚዛን ጠብቆ እየተጓዘ የሚገኘው የለውጡ መንግስት ከፉክክር ይልቅ ትብብርን እንደሚያስቀድም አስገንዝበዋል።

ሰላም የሰፈነባት የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተደራጀና በተቀናጀ የህዝብ ግንኙነት ስራና የሀሳብ ትግል ፅንፈኝነትን መግራት እንደሚገባ / ሚኤሶ አሳስበዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት የምሁራንና የከፍተኛ ተቋማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይቻላል አይኔ ስልጠናው የታችኛው መዋቅር አመራር የብልፅግና ፓርቲን ህገደንብ፣ አሰራርና መመሪያ በሚገባ እንዲያውቅና በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዝ በማድረግ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ማጎልበትን ዓላማው ያደረገ መሆኑን ገልፀውልናል።

ለሁሉም ሕዝቦች የሆነች ሀገር ከገነባን ኢትዮጵያ በቂ ናት፤ ያለው አላስፈላጊ ሽሚያ ግን ጥፋት ያመጣል።

ጠቅላይ ሚኒስትር / ዐቢይ አሕመድ

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300556
Total Visitors