May 2

July 23, 2023

በአዲስ አበባ ከተማ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዥ የወጣቶች ተሳትፎ ንቅናቄ ተጀመረ
በአዲስ አበባ ከተማ “እኔም ድርሻ አለኝ!!” በሚል መሪ ቃል ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ ግዥ ወጣቶች ተሳትፎ የሚያደርጉበት ንቅናቄ የከተማዋ አመራሮችና ወጣቶች በተገኙበት ተጀምሯል።
በከተማዋ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪነት የተጀመረው የወጣቶች የቦንድ ግዥ ንቅናቄ መድረክ ላይ የተገኙት የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፉት መልዕክት የአብሮነታችንና የወንድማማችነታችን መገለጫ ለሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ወጣቶች በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
የከተማዋ ወጣቶች አጠቃላይ 85 ሚሊዮን ያህል ብር ለማሰባሰብ በማቀድ ወደ ተግባር የገቡ መሆናቸውን በመግለጽ የዛሬውን የንቅናቄ ፕሮግራም ከመጀመሩ አስቀድመው ወጣቶቹ 20 ሚሊዮን ብር ማሰባሰባቸውን በማድነቅ በዕቅዳቸው የያዙትን ቀሪ 65 ሚሊዮን ብር የማሰባሰብ ተግባርም በስኬት እንደሚያጠናቅቁት ያላቸውን ተስፋ አቶ በላይ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ በበኩላቸው ሀገራችን በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ቢሆንም በውስጣዊ እና ከውጭ በሚመጡ ችግሮች ሳንጠቀምባቸው መቆየታችንን አስታውሰው የለውጡ መንግስት የህዳሴ ግድባችንን በተሻለ መልኩ ከማስቀጠሉ በተጨማሪ የተፈጥሮ ሀብታችንን ጥቅም ላይ ለማዋል አበረታች ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በዛሬው ዕለት በንቅናቄ በተጀመረው የቦንድ ግዥ ተሳታፊ በመሆን የከተማችን ወጣቶች የልማት ሃይል መሆናቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ በተፈጥሮ ሀብታችን የመጠቀም የዘመናት ቁጭት ወደ ደስታ እየተቀየረ መሆኑን በመግለጽ የለውጡ አመራር የህዳሴው ግድብ የነበረበትን መጠነ ሰፊ ችግር በማረሙ የግድቡ ግንባታ ወደ መገባደዱ መቃረቡን አብራርተዋል።
ከ2011 ወዲህ ብቻ የከተማችን ህዝብ በቦንድ ግዥና በድጋፍ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ለግድቡ አስተዋፅኦ ማድረጉን የጠቆሙት ሀላፊው ግንባታው 90 በመቶ አካባቢ ቢጠናቀቅም በርካታ ወጪ የሚጠይቁ ስራዎች ከፊታችን ስለሚጠብቁን ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
በንቅናቄ መድረኩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን የቦንድ ግዥ ማስጀመሪያ ንቅናቄውን ወጣቶቹ ቦንድ በመግዛት አስጀምረውታል።

 

“ኢትዮጵያ ወደ ዳገት ጉዞ ላይ ነች ያለችው፤ ወደፊት በጣም ቅርብ ነው፤ የሚታይ ቢሆንም ግን ከባድ ነው፡፡ ወደ
ኋላ መመለስ በጣም ሩቅ ነው ግን ቁልቁለት ስለሆነ ቀላል ነው፡፡ ከፍተኛ ጉልበት፣ አንድነት እና ትብብር ይጠይቃል፡፡ ከአቅም በላይ ተባብረን መግፋት ይፈልጋል፡፡”
– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

 

የለሚ እንጀራ ማዕከል እውነታዎች
* 1.1 ሄክታር ላይ ያረፈ ማዕከል ነው
* እንጀራን ኢንዱስትራላይዝ በማድረግ በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነ ማዕከል ነው
* ግንባታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተባባሪነት በ90 ቀን ሰው ተኮር ፕሮጀክት የተገነባ ፕሮጀክት ነው
* በዚህ ፕሮጀክት ጀምሮ መጨረስ፣የምንናገረውን በተግባር የማዋል እና 24 ሰዓት በመስራት የስራ ባህል ማሻሻል የታየበት ነው
የእንጀራ ማዕከሉ ከ12 በላይ ብሎኮች ያሉትና በውስጡ፡-
* የአስተዳደር ህንፃ፣ ቢሮና ሌሎች ፋሲሊቲዎችን ያካተተ
* ሰፊ የጤፍ ስቶር (መጋዘን) ያለው፣
* የማበጠሪያና ዘመናዊ ወፍጮ ያለው፣
* እያንዳንዳቸው 250 ምጣድ የተገጠመላቸው አራት እንጀራ መጋገሪያ ብሎኮች ያሉት
* የእንጀራ ማቀዝቀዣ፣ ማሸጊያና ስቶር ያለው፣
* የወንዶች ማረፊያ ሻወርና መፀዳጃ ያለው
* የሴቶች ማረፊያ ፣ ሻወር፣ የልጆች ማቆያ (ዲይ ኬር) ያለው፣
* እራሱን የቻለ ካፍቴሪያ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የመዝናኛ ሜዳ ያለው፣
* ለነዋሪው አገልግሎት የሚሰጥ ሰፊ ፓርክ
* በዚህ ፕሮጀክት የአካባቢው እናቶችና ሴቶች ፣ ስራ የሌላቸው አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች ፣ በተለያየ ምክንያት ይዞታቸውን ያጡ ፣ በመልሶ ማልማት ምክንያት ከማሃል ከተማ ተነስተው ለዝቅተኛ ነዋሪዎች በተገነባ 10/90 ውስጥ ያሉ ስራ የሌላቸው እናቶች እና ሴቶች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
* የእንጀራ ማዕከሉ 288ሺህ እንጀራ በቀን በሁለት ሺፍት መጋገር ይችላል፡፡
* ማዕከሉ ለትልልቅ ድርጅቶች፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ኤክስፖርት ማድረግ የሚያስችል አቅም ያለው ነው
* ማዕከሉ ከ2000 እናቶች በተጨማሪ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ1000 ነዋሪዎች በጠቅላላው 3000 ለሚሆኑ ወገኖች የስራ እድል የሚፈጥር ነው
* ማዕከሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ በዙሪያው ካሉ አጎራባች ከተሞች ጋር ግብዓትና የገበያ ትስስር በመፍጠር ማህበራዊ መስተጋብር የሚፈጥር ነው፡

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300480
Total Visitors