May 1

July 23, 2023

“በየቦታው ያለንን አቅም፣ ገንዘብ እና እውቀት በማስተባበር የነዋሪዎችን ሸክም የሚያቀሉ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እየተገበርን ነው!!”
– የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት
“በቀን 288 ሺህ እንጀራ የሚጋገርበትና እንጀራን ኢንዱስትራላይዝ በማድረግ በሃገራችን የመጀመሪያውን ማዕከል ገንብተን ከመላው የሀገራችን ከተሞች ከመጡ ከንቲባዎች ጋር በመሆን መርቀናል::
እንጀራን ኢንዱስትራላይዝ በማድረግ በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነው ለሚ እንጀራ ማዕከል የእናቶችን ድካም የሚያቀልና እንጀራን ከፍ ባለ ደረጃ ማምረት የሚያስችል ማዕከል ሲሆን ከፈተናዎቻችን በላይ ሆነን የማይቻል የሚመስለውን የመቻላችን ማሳያ ነው።
በየቦታው ያለንን አቅም፣ ገንዘብ እና እውቀት በማስተባበር የነዋሪዎችን ሸክም የሚያቀሉ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እየተገበርን ሲሆን የእንጀራ ማዕከሉ ከ2000 እናቶች በተጨማሪ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ1000 ነዋሪዎች በጠቅላላው 3000 ለሚሆኑ ወገኖች የስራ እድል የሚፈጥር ነው::
በዚህ የእናቶችን ሸክም በዘላቂነት በሚያቀልለው ታላቅ ስራ ላይ ያገዙን ልበቀና ባለሃብቶችን በተለይም ፦
1. ኦቪድ ግሩፕ 170 ሚሊዮን
2. ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 75 ሚሊዮን
3. መድህን ድርጅት 20 ሚሊዮን ብር
4. መታሰቢያ ታደሰ ኮንስትራክሽን 500 ዘመናዊ ምጣዶችን በማቅረብ
5. የታፑ ምግቦች በማማከር ሁሉንም በእናቶቹ ስም አመሰግናለሁ።”

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300588
Total Visitors