May 1 “የጋራ አስተሳሰብ በመያዝ የትምህርት ጥራትን እናረጋግጣለን !!”

July 23, 2023

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 63 ሺህ በላይ የሚሆኑ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት መምህራን ባለፉት ሶስት ቀናት ሲደረግ የቆየው ውይይት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ / አዳነች አቤቤ፣ የከተማው ብልፅግና /ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ / ዘላለም ሙላቱ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጠቃለለ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የለውጡ መንግስት ከመጀመሪያው ጀምሮ ለሰላም ብዙ ርቀት መጓዙን ጠቅሰው በቅርቡምየአፍሪካን ችግር አፍሪካዊ መፍትሄበሚል የተጀመረው የሰላም ጥረት ለሌሎች ሀገሮችም ምሳሌ በሚሆን መልኩ ውጤት እያሳየ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር በማድረግ በሀገራችንና በከተማችን የተደቀኑ ፈተናዎችን እንድንሻገር የከተማችን ትምህርት ቤቶች እያበረከቱት ያለውን ጥረት ያደነቁት ከንቲባዋ የአገራችንን ብሩህ ተስፋ ለትውልዱ በማሳየት እንዲሁም በእውቀትና በምግባር ትውልዱን በመገንባት ለትውልድ ቅብብሎሹ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የመምህራንና የሌሎችንም የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ችግር ለመቅረፍ ባለሀብቱን በማሳተፍ የቤት አቅርቦቱን ለማሳደግ እና በተለያዩ አማራጮች ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን የገለፁት / አዳነች በማህበር ተደራጅተው የቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችለውን የቤት ልማት ፕሮግራም ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የከተማችንና የሀገራችን ልማትና ብልፅግና አጠናክሮ በማስቀጠል የመምህራንንም የሁሉንም ህዝባችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ በእንችላለን መንፈስ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያስገባና መጪውን ትውልድም ታሳቢ ያደረገ ሆኖ የመሀሉን መንገድ የሚከተል በመሆኑ በፈተና ውስጥም ጭምር የትምህርት ዘርፉን ጨምሮ በሁሉም መስክ ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

መምህራን ትውልዱን በመልካም ስነምግባር የማነፅ ሀላፊነት እንደተጣለባቸው የገለፁት አቶ ሞገስ ትልቁ የሀገራችን ፈተና የሆነውን ፅንፈኝነትን በመታገል ለብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማነት የድርሻቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

መምህራን ለብዝሀነት መከበር ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ያስረዱት ሀላፊው ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ እና በትምህርት ቤቶች ሴኩላሪዝም በአግባቡ እንዲተገበር የተጀማመሩ ጥረቶችን አጠናክረው

እንዲያስቀጥሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላት በበኩላቸው ሀገር በዜጎች፣ ዜጎች ደግሞ በመምህራን እንደሚገነቡ ገልፀው ቢሮው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገውን የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ መሰረት አድርጎ በትምህርት ቅበላ እና ተሳትፎ እንዲሁም ጥራትን በሚያሻሽሉ ጉዳዮች ላይ ከከተማው አመራር ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

መምህራን መቻቻልን፣ መከባበርን ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በማስተማርና ምሳሌ በመሆን ሀላፊነታቸውን መወጣታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት አቶ ዘላለም ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩና የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሻሻል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስገንዝበዋል።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300463
Total Visitors