App 29

July 23, 2023

በጥይት ሰውን እንጂ ሀሳብን መግደል አይችሉም !!ፅንፈኝነት ይብቃ
ፅንፈኝነት በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር ይገለፃል። ፅንፈኝነት መጀመሪያ በሃሳብ ይታያል፣ እናም ቀስ በቀስ ወደ ተግባር ይሸጋገራል።ስለሆነም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በመንቃት የፅንፈኝነት ሃሳቦችን እና አመለካከቶችን በማጥፋት ከሃሳብ አልፎ ወደ ተግባር እንዳይሸጋገር ማድረግ ያስፈልጋል።ፅንፈኝነት የሀሳብ፣ የአመለካከት፣ የማህበራዊ ግንኙነት እና የህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት ልዩነቶችን እንደ ችግር ይወስዳቸዋል። በህዝቦች መካከል ፍቅርና ሰላም እንዳይኖር ሁሌም ጠንክሮ ይሰራል።ፅንፈኞች ይዘው የምንቀሳቀሱት ሃሳቦች የህዝቡን ችግር የሚፈታ፣ የግንባታ ሃሳቦች፣ የወንድማማችነት ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ሃሳቦች እና የልማት ሃሳቦች አይደሉምና ማስተዋል የጎደላቸውና ተስፋ የቆረጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሊቀበሉት ይችላሉ። ፅንፈኞች ወደ ውይይት መድረክ በመውጣት እና ሃሳብን በሃሳብ በማሸነፍ በማሳመን ማመን ሽንፈት ነው ብለው ያስባሉ። ይህ ማለት ምክንያታዊ ያልሆኑ መረዳት የማይችሉ እና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ የግል ቅሬታ ያላቸውን ሰዎች በመለየት፣ ለድርጊታቸው ፈጻሚ ያደርጋሉ።በሌላ በኩል ህዝቡ ሃሳቡን ተቀብሎ እንዲከተል ለማድረግ የጥላቻ ዘመቻዎችን፣ ስም ማጥፋትን አልፎ ተርፎም የጦር መሳሪያ ሃይልን እንደ ስልት ይጠቀማሉ። ፅንፈኞች በህዝቡ መካከል ፍርሃትና ጭንቀት መፍጠር እንደ ስልት ወስደው ለድርጊታቸው ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ ሀሳብን በሀሳብ ማሸነፍ የማይችሉ ሰዎች ምልክት ነው፤ ዋና አላማቸው ሰላምን ማደፍረስ፣ ህዝብን ማሸበር፣ የጸጥታ ተቋማትን እና የመንግስት መዋቅሮችን ማፍረስ፣ የህዝብን ሞራል፣ ባህልና ወግ ማጥፋት ነው።ለዚህም ነው ፅንፈኝነትን መቃወም የሁሉም መለኪያ ሊሆን የሚገባው። የፅንፈኞችን ሀሳብና አመለካከት ማምከን፣ ሃሳባቸው ወደ ተግባር እንዳይቀየር መከላከል፣ የሀገርና የህዝብን ደህንነትና መረጋጋት ማረጋገጥ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው። ይህን ማሳካት የሚቻለው ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት በማጠናከር ነው።
ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት / እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ልማት !!
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ልዑክ ወደ መቀሌ ገብተዋል።
የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮቹ እና የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በመቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመቀሌ ከተማ ነዎሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የርዕሳነ መስተዳደሮቹ የመቀሌ ጉዞ ለትግራይ ክልል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና በመልሶ ግንባታ ሂደት የድርሻውን ለማበርከት ዓላማ ያደረገ ነው።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
299143
Total Visitors