May 13

July 10, 2023

1, ሴቶች ለብልፅግና፤ ብልፅግና ለሴቶች !! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርሴቶች ለብልፅግና፤ ብልፅግና ለሴቶች!!” በሚል ትኩረቱን በሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ ያደረገ ከተማ አቀፍ የሴቶች የውይይት መድረክ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተከናወነ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማዋ ብልፅግና ፓርቲ /ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም 15ሺህ በላይ የሆኑ የውይይቱ ተሳታፊ ሴቶች ተገኝተዋል።

ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን !!

2, “አፍሪካ የአያሌ ሃብቶችና ፀጋዎች ምድር ናት። እነዚህን ሃብቶች ወደ ተጨባጭ የብልፅግና ዓቅም ለመቀየር የአፍሪካ የሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ ምትክ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ ነው። ለዚህም ሁላችንም የጋራ ኃላፊነት አለብን። ከሁሉ በላቀ ደግሞ የአፍሪካ የመከላከያ አዛዦች፣ የሰላምና ፀጥታ አመራሮች ይህን ወሳኝ ሚና መጫወት አለባቸው

3, ጠቅላይ ሚኒስትር / ዐብይ አህመድ

በፍራፍሬ፤ በዶሮ፤ በሥጋ፤ በወተት፤ በስንዴ፤ በማር ያየነው ዕድገት ተስፋ ሰጪ ነው። ግን ይሄ በገጠርም በከተማም ተሳሥሮ እንዲስፋፋ ሁሉም ሰው ግብርና የሕይወታችን አካል፤ የዕለት ተለት ኑሮ አካል መሆኑን መገንዘብ አለበት። ውኃን፤ መሬትን፤ ጉልበትን በመጠቀም እንዴት ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል ማሰላሰል ይገባናል።” 

ጠቅላይ ሚኒስትር / ዐቢይ አሕመድ

የነገይቱን ኢትዮጵያ የሸፈናት አቧራ ተራግፎ፤ እውነተኛ ውበቷ ጎልቶ መውጣት አለበት። አዲሱ ትውልድ የተፈጥሮ ጸጋዎች ለምተውና ተጠብቀው፤ ለዓይን ከሚማርኩ ሰው ሠራሽ መሠረተ ልማቶች ጋር ተሳልጠው፤ ድንቅ ውበትን የሚያጎናጽፍ እንዲሆኑ ይሰራል። ሀገራችን ጥንታዊነትና ዘመናዊነት፤ እንዲሁም ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ውበቶች በአንድ ላይ የተዛመዱባት የማራኪ ገጽታ ባለቤት እንድትሆን፤ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን መስራት ይኖርብናል። ያኔ ነባር ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መስሕቦቻችን ከዘመናዊ ኪነ ሕንጻዎችና ወቅታዊ ስልጣኔዎች ጋር ተዋድደው ልዩ ውበትን ይፈጥራሉ።

#የመደመርትውልድ

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
300655
Total Visitors