May 12

July 10, 2023

በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ለሚገኙ የህዋስ አባላት በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት፣ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ማስተባበሪያ ዘርፍ ሀላፊ / ሚኤሶ ኤለማ በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ህብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ በሰጡት ስልጠና ብልፅግና ፓርት በሀገር አንድነትና በብዝሃ ማንነት መካከል ያለውን የህብረ ብሔራዊነት ሚዛን ጠብቆ እየተጓዘ መሆኑን በመግለጽ ኢትዮጵያ ባላት ነባራዊ ሁኔታ አንዱ የበላይ የሚሆንበት፣ አንዱ ደግሞ ብቻውን ተገንጥሎ በሰላም የሚኖርበት ዕድል እጅግ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ብዝሃ ማንነቶችን አክብሮ በአንድነት መጓዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዘመኑን የሚዲያ አማራጮች ሁሉ በመጠቀም ለህብረ ብሔራዊ አንድነታችን መጎልበት የድርሻውን መወጣትና ራሱን ከፅንፈኝነት ማራቅ እንደሚገባውም ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት የምሁራንና የከፍተኛ ተቋማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይቻላል አይኔ በበኩላቸው ብልፅግና በመጀመሪያው ጉባኤ ወቅት ያፀደቀውን የፓርቲን መተዳደሪያ ደንብ፣ የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያ ለሰልጣኞቹ ያቀረቡ ሲሆን ሁሉም አባላት የብልፅግናን መርህ እና እሴቶች አውቆ መንቀሳቀስና ሞዴል ህዋስ ለማበራከት የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በመደመር ፓራዳይም የተቃኘው የኢትዮጵያ ብልፅግና፤ ቀዳሚ የዓለም ስልጣኔ የሆነው የአፍሪካ ስልጣኔ እንደገና እንዲያንሰራራ ቀስቃሽ ኃይል ነው። ይኽ ተምሳሌተ አፍሪካ ስልጣኔ፤ ነባራዊ ሁኔታዎችን የተገነዘበና አፍሪካዊ እሴቶችን አንግቦ አፍሪካዊ ለውጥ ለማምጣት የሚተልም ነው። በዚህ የፖራዳይም ለውጥ የተቃኘው ትውልድ፤ ፓን አፍሪካኒዝም እሴቶችን የሚላበስ፤ የቀደመውን ዘመን የአፍሪካን የነጻነት ትግል ከመሩ ንቁ ወጣቶች ጋር የሚመሳሰል ትውልድ ነው። የአፍሪካን የአዲስ ዘመን ብልፅግና የሚመራውም እርሱ ነው።

#የመደመርትውልድ

 

ቡብዝሃነትን ማስተናገድ ህብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ ነው !!

ብልጽግና ፓርቲ በወንድማማችነት/እህትማማችነት እሴት ላይ የተመሠረተ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት አበክሮ እየሠራ ይገኛል። 

ብልጽግና ፓርቲ ትኩረት የሚያደርገውና ሊያሳካ የሚፈልገው ብዝሃነትን የሚቀበልና የሚደግፍ ሥርዓት መፍጠር እና በዚያው ልክ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ጠንካራ የሚያደርግ ሥርዓት መገንባት ላይ ነው፡፡ 

ፓርቲው የፌደራል ሥርዓቱ ዋና መሰሶ ብዝሃነትን ማስተናገድ መቻሉ ነው ብሎ ያምናል፤ በመሆኑም ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እውቅና የሰጠ የፌደራሊዝም ሥርዓት በመገንባት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት የተከበረባት እውነተኛ ህብረብሔራዊት ፌዴራሊዝም የተገነባባት ሀገር ለመፍጠር ይሰራል፤ እየሰራም ይገኛል።

የቡድንና የግል መብቶች፣ ማንነትና ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀው የሚስተናገዱበት፣ በራስ አስተዳደር እና በጋራ አስተዳደር ማዕቀፍ የተቀመጡ መብቶች የሚከበሩበት የፌደራሊዝም ስርዓት እውን ማድረግ የትኩረት ማዕከል ነው።

መልካም ቀን ይሁንልዎ !!

እንችላለን

ኢትዮጵያ ማምረት ትችላለች። ኅብረትን፤ ልማትን፤ አንድነትን ገንዘብ ካደረግን። በቂ መሬት፤ በቂ ውኃ፣ ሊያመርት የሚችል በቂ ወጣት፤ ምርትን መደገፍ የሚችል ኢነርጂ፤ በንጽጽር ሻል ያለ የፋይናንስ አቅርቦት፤ አስቻይ የሆነ የማምረቻ ዐውድ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉን። ግብዐቱ አለን፤ በማዕድን ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች ለኢንዱስትሪው በከፍተኛ ደረጃ ግብዐት መሆን ይችላሉ፤ በግብርና ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎች በከፍተኛ ደረጃ ለኢንዱስትሪው ግብዐት መሆን ይችላሉ፤ ከፍተኛ የማደግ ፍላጎት አለን። ስለዚህም የልማትን ምርት ማረጋገጥ እንችላለን!

 የብልፅግና ጉዟችን እንዲሰምር

በመደመር እሳቤ እንጓዝ !!

ወንድማማችነት / እህትማማችነት የማይተካ መርሃችን ይሁን !!

ትጋት እና ብርቱነት ከእኛ አይለይ !!

ውስጣዊ አንድነታችን እናጠናክር !!

ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያልተሰሩ ቀሪ ስራዎችን ለመስራት የሚታትር ህዝባዊ ፓርቲ ብልፅግና !!

ፓርቲያችን ብልፅግና እየተገበረ በሚገኘው በመደመር እሳቤ የተቃኘ የብልፅግና ጉዞ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሀገሪቱ በሚካሄደው ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ 

በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ መሰረታዊ ተግዳሮቶችን መፍታት እንዲቻልም ለመብቱና ለልማቱ ተጠቃሚነት የሚታገል ሞጋች ህብረተሰብ በመፍጠር ሂደት ላይ ቀጣይነት ያለው ስራ እየሰራ የሚገኝ አሳታፊ ፓርቲ ነው፡፡

በመላው ሀገራችን የህዝቡን ሁለንተናዊ የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ ሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም በፖለቲካው መስክ ንቁ ተሳታፊ እና በኢኮኖሚውም ቢሆን የዳበረ ሀገር ለመፍጠር ተግቶ እየሰራ የሚገኝ ተራማጅና ፓርቲ ነው ብልፅግና፡፡

ፓርቲያችን ኢትዮጵያን በሀላፊነት ተረክቦ ማስተዳደር ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ባስመዘገባቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ሁሉን ዓቀፍ ለውጦች የተነሳ በሀገሪቱ የታሪክ መዝገብ ውስጥ መስፈር የሚያስችል ዕውቅናን ከመላው የሀገራችን ህዝቦች፣ ከአፍሪካም ይሁን ከመላው ዓለም ማግኘት የቻለ ባለራዕይ ፓርቲ ነው፡፡

ብልፅግና በቂ ለውጥ አምጥቻለሁ በማለት ራሱን የጀግንነት ካባ የማያለብስ፤ ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያልተሰሩ የቤት ስራዎችን ለመፈፀም ያካበተውን ህዝብን የማስተባበር ልምድ ተጠቅሞ ውጤት ለማምጣት ሌት ተቀን የሚጥር እና ለዚሁ ስራ እንቅፋት የሚሆኑ ውስጣዊ ድክመቶቹን በመፈተሽ ራሱን ማስተካከል የሚችል 12 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ግዙፍ ፓርቲ ነው፡፡

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
304111
Total Visitors