ወጣቱ ትውልድ ዋነኛ የብልፅግና ባለቤት ነው!

July 10, 2023

አቶ ሞገስ ባልቻ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ ቅርንጫፍ /ቤት በየደረጃው የሚገኙ አመራርና አባላት በሊጉ 2015 . በጀት ዓመት የስድስት ወራት አፈፃፀም እና የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ተወያዩ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም የሀገራችን ህዝብ በእኩል ዓይን የሚያይና ለኢትዮጵያ ብልፅግና ሌት ተቀን የሚተጋ መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ / / ዐብይ አህመድየመደመር ትውልድብለው የሚጠሩት ወጣቱ ትውልድ ዋነኛው የብልፅግና ቤተሰብና ባለቤት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ለተያዘው ራዕይ ስኬታማነት ከወጣቶች ተጠቃሚነት አንፃር እየቃኙ የትግል ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ሞገስ የተለያዩ አስተሳሰቦችና ፕሮግራሞች ባሏቸው ፓርቲዎች የታቀፉ ወጣቶችም በሀገራዊ ጉዳዮች የድርሻቸውን እያበረከቱ እንዲጓዙ የሊጉ አባላት ቅመምና ጨው ሆነው በአርያነት እንዲንቀሳቀሱ ጠይቀዋል።

የሊጉ አባላት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር የከተማችንን ወጣቶች በማስተባበር ሚናቸውን መወጣታቸውንና ፈጣሪ የሰጣቸውን የወጣትነት ጉልበት በበጎ ፈቃደኝነት አረጋውያንንና አቅመ ደካሞችን ለመርዳት እያደረጉት ያለውን ጥረት ያደነቁት አት ሞገስ ዛሬ የምትሰሩት መልካም ስራ ነገ ይከፍላችኋልና አጠናክራችሁ ቀጥሉ በማለት ለምታከናውኑት በጎ ዓላማ አስፈላጊው ድጋፍም እንደማይለያቸው መልዕክታቸውን ለወጣቶች አስተላልፈዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ በበኩላቸው ውይይቱ የስድስት ወራት አፈፃፀም ጥንካሬዎችን ለማስፋት እና ድክመቶችን ለማረም እንዲሁም የሊጉን ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔዎች መሬት ለማውረድ እንደሚያስችል አስረድተዋል።

የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለመጨመር እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ሊጉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት ወጣት መለሰ የወጣት ሴቶች የስራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ ተሳትፎም 50 በመቶ መድረሱን ጠቅሰዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለይም በከተማችን ባህል ወደ መሆን ደረጃ እያደገ መሆኑን የገለፁት ወጣት መለሰ ወጣቶችን መጠቀሚያ ለማድረግ ከተለያዩ አካላት የሚረጩ የፅንፈኝነት አስተሳሰቦችንና አመለካከቶችን በመመከት የከተማችን ልማትና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ ቅርንጫፍ /ቤት /ኃላፊ ወጣት በቀለ ታጀበ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚሳካው በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በመሆኑ ሊጉ የማስተባበር ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ከወረዳ ጀምሮ ያለውን መዋቅር የማጠናከር ተግባር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አብራርተዋል። 

ህብረብሔራዊ እህትማማችነትንና ወንድማማችነትን ማጠናከር፣ ለወጣቶች ተጠቃሚነት በልዩ ትኩረት መስራት፣ በጎ ፈቃደኝነትን ማጠናከር፣ ሚዲያ ለሀገር ግንባታና የህዝብን አንድነት ለማጠናከር እንዲውል መስራትና የተጀመረውን የተቋም ግምባታ እንቅስቃሴ ማጎልበት ሊጉ ከቀሪ ወራት ዕቅዱ ጋር አስተሳስሮ እንደሚያከናውን የሊጉ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት አንሙት አበጀ ባቀረቡት ሪፖርት ተገልጿል።

የከተማችን ልማት በማፋጠን የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ ወጣቶችን በማስተባበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

# ፅናት

ፓርቲያችን ብልፅግና በጉባኤ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች በፅናት እየተተገበሩ ይገኛል።

ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የጎላ ፋይዳ እንዳለው በማመን ሁሉም እኩል ተሳታፊ የሚሆንበት አንድ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ገና ከምስረታው ጀምሮ ካጋጠሙት ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ነጥሮ በመውጣት ለህዝባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል።

በፓርቲያችን ውስጥ ይታይ የነበረው የጎራ መደበላለቆች እየጠሩ በአንፃሩም የጋራ መስተጋብሮች እየተጠናከሩ ሲሆን አመራሩ ከሌብነት የፀዳ የአገልጋይነት መንፈስ እንዲላበስም አበረታች እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛል።

ፓርቲያችን ብልፅግና በመጀመሪያው ታሪካዊ ጉባኤ የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ በማስፋት እና በማጽናት የህዝባችንን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የገባውን ቃል በፅናት መተግበር መጀመሩን ሁሉም ይረዳዋል።

ለአብነትም በከተማችን አዲስ አበባ ብሔርንና ሀይማኖትን የፅንፈኝነት እና የሌብነት መሸሸጊያ ለማድረግ የሚጥሩ አካላትን ህዝባችንን በማሳተፍ አስተማሪ የህግ እርምጃ በማስወሰድ ተጠያቂነትን በማስፈን እንዲሁም የከተማችን አስተማማኝ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶ በየዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶች የዚህ ማሳያ ናቸው።

በሰው ተኮር ስራዎቻችን የሀገር ባለውለታዎችን እና አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ከከተማዋ ዕድገት ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን !!”

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
303898
Total Visitors