በጎነት ከራስ የሚመነጭ፣ ለሌሎች መትረፍ፣ ከተረፈን ሳይሆን ካለን ላይ የምናካፍለው በፈጣሪም፤ በሰውም ዘንድ የሚወደድ ተግባር ነው !!

July 10, 2023

አቶ ሞገስ ባልቻ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ //ቤት ኃላፊ መልዕክት

በጎነት ከራስ የሚመነጭ፣ ለሌሎች መትረፍ፣ ከተረፈን ሳይሆን ካለን ላይ የምናካፍለው በፈጣሪም፤ በሰውም ዘንድ የሚወደድ ተግባር ነው።

ይህን በጎ ተግባር በከተማችን አዲስ አበባ በክረምቱ ወራት አጠናክሮ ለማስቀጠል በዛሬው ዕለትበጎ ፍቃደኝነት ለዘላቂ አብሮነት !!” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ባለፊት ጊዜያት በነበሩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ለህብረተሰባችን ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ተቋማት በከተማችን ነዋሪ ስም የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራምም አከናውነናል።

አሁንም ይህ የበጎ ፍቃድ ስራ በከተማችን ዘላቂ እንዲሆን በጎ አድራጊ ግለሰቦችን እና ተቋማትን በማስተባበር የዜጎቻችንን ህይወት ሊቀይሩ የሚችሉ ተግባራትን በማከናወን እና የከተማችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ በጋራ በመሆን እንሰራለን !!”

አዲስ አበባችን፤ የብልፅግና ማሳያችን !!

የበጎነት ተግባር በቀናነት ለተባበራችሁንና ላስተባበራችሁ እንዲሁም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምስጋናችን ይድረሳችሁ

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት

2014 እና 2015 . የክረምት ወራት በበጎ ፈቃድ ስራዎች ከጎናችን ለተሰለፉ በጎ ፍቃደኞች እውቅና ሰጥተናል። በነዋሪው ስም ስለበጎነታቸውም አመስግነናቸዋል።

በበጎ ፍቃድ ስራዎቻችን የበርካቶችን እንባ አብሰናል፤ የኑሮ ጫናዎቻቸውን አቅልለን የጨለመ በመሰለው ኑሯቸው የተስፋ ጮራ ፈንጥቀናል።

ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ከከተማቸን ዕድገት ፍትሀዊ ተጠቃሚ በማድረግ ማህበራዊ ፍትህ የማንገስ ታላቅ ስራ ሰርተናል። በዚህ ታላቅ የበጎነት ተግባር በቀናነት ለተባበራችሁንና ላስተባበራችሁ እንዲሁም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

ለከተማችን ታላቅነት የላቀ አስተዋጽዖ ያላቸውን ታላላቅ ፕሮጀክቶች በገባነው ቃል መሠረት በጥራትና በጊዜ እየገነባን የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ሸክም የሚያቀልሉ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሠራን ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን መገንባታችንን እንቀጥላለን።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
303917
Total Visitors