ሞገስ ባልቻ

July 10, 2023

የብልጽግናን ጉዞ አፋጥኖ ዕውን ለማድረግ በነዚህ ስጋቶች ዙሪያ የሚደረገው ዝግጅት ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ስራ በመስራት የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ለመቋቋም ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች ብለዋል።

ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር ተያይዞ ጥቅሙን ከመውሰድ ባለፈ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ የሚያስችል ስራና በተቋም ግንባታ ሂደት የሚመለከታቸው ተቋማት ጠንካራ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

አንድነታችንን አጠናክረን ለመሄድና የብልጽግና ጉዞውን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ሀገራዊ ምክክርና መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህ ሂደት የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የሀገረ መንግሥት ግንባታና የብልጽግናን ጉዞ ከፍ ባለ ውጤታማነት ማስቀጠል የሚቻልባቸው ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
303775
Total Visitors