ሀገራዊ እሳቤዎቻችንን እና ሀብቶቻችንን በአግባቡ በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ትልቅ አቅም አለን!!

July 10, 2023

አቶ አደም ፋራህ 

የብልጽግና ፓርቲ /ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ 

ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ ያላት ሀገር ነች። ሀገራችን የልማት ጉዞዋን በጀመረችው አግባብ ከቀጠለች የብልጽግና ግባችንን ዕውን እንደምናደርግ የሚያሳዩ ሶስት መሰረታዊ አቅሞች አሉ።

የመጀመሪያው ጉዳይ እሳቤዎቻችን ላይ ያተኩራል ያሉት አቶ አደም፤ እንደሀገርም ሆነ እንደ ፓርቲ ሀገር በቀል የሆኑ የኢትዮጵያን ብልጽግና ዕውን ማድረግ የሚያስችሉ ግልጽና ጥራት ያላቸው እሳቤዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ዕውን መሆን የሚያስችሉ ሀብቶች አሏት። አጠቃላይ የሰው ሀብታችን፣ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጣችንና የተፈጥሮ ሀብታችን ለብልጽግናችን ዕውን መሆን ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው ብለዋል። እሳቤዎቻችንን እና ሀብቶቻችንን በአግባቡ ማየት ከቻልን ኢትዮጵያ ለመበልጸግ ትልቅ ዕድል ያላት ሀገር መሆኗን በአግባቡ እንረዳለን። እሳቤዎቻችንና ሀብታችንን ለመጠቀም ደግሞ በሶስተኛነት ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት እሳቤዎቻችን የጠሩ፣ የኢትዮጵያን መሰረታዊ ሁኔታዎች ተጨባጭ ያደረጉና ኢትዮጵያን የሚያበለጽጉ እንዲሆኑ ሰፊ ስራ ተሰርቷል። ሀብቶቻችንን በአግባቡ ለማወቅና ለመጠቀም የሚያስችሉ አቅጣጫዎችንም መከተል ጀምረናል ብለዋል። በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የተፈጥሮ ሀብታችንን መጠቀም እንደምንችል አሳይተናል።

ሶስተኛው ጉዳይ ልማቶቹን በውጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችል አመራር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያን የሚወድ፣ ቁርጠኛና በፈተናዎች የማይሸነፍ አመራር አለ።

ፈተናን ወደ ዕድል የሚቀይር፣ በጊዜ የለንም መንፈስ የሚሰራ ውጤታማም አመራር አለን። ስለዚህ እሳቤውን፣ ሀብታችንን እና የአመራር ጥበብን በጥምረት ስናይ ኢትዮጵያ በትክክልም ተስፋ አላት ብለን መናገር እንችላለን ሲሉ አስረድተዋል።

ብልጽግና መሰረት የሚጥሉ ጉዳዮች እየተገነቡ ይገኛሉ። የዴሞክራሲና የነፃነት ልምምዱ እየተጠናከረ ሄዷል ባለፉት ሥርዓቶች በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎች ነበሩ። በተለይ የኢኮኖሚ፣ የብሔሮች መብት እኩልነት እንዲሁም የዴሞክራሲ ጥያቄ መታየቱን አስታውሰዋል።

የዴሞክራሲ ባህሉ እና የትብብር እሴት ስላልተገነባ የኢኮኖሚውም ሆነ የብሔሮች ጥያቄ በአግባቡ ሳይመለስ መቆየቱን ጠቁመዋል።

ከለውጡ በኋላ ግን የዴሞክራሲ ባህልን የሚገነቡ ሰፋፊ ስራዎች ተከናውነዋል። የዴሞክራሲ ልምምዶቹም በርካታ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ መሰረት የጣሉ ናቸው። የተቋማት ግንባታና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶበት ተሰርቷል። ተቋማትን በአመራር፣ በአደረጃጀት፣ በአሰራርና በቴክኖሎጂ ብቁ እንዲሆኑና የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል።

ለሀገረ መንግሥት ግንባታና ብልጽግና የተቋማት ግንባታ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት የተሰጠው ስራ ነው። በተጨማሪ ብልጽግናን ዕውን የሚያደርጉና በአጭር ጊዜ ይገነባሉ ተብለው የማይታሰቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል።

አዲስ አበባ ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የቱሪስት መዳረሻዎችና የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት ተሰርተዋል። በተመሳሳይ የዘገዩ ነባር ፕሮጀክቶችም በተሻለ ፍጥነትና ውጤታማነት እንዲገነቡ የተደረገበት አቅጣጫ የብልጽግና ጉዞውን አመላካች ናቸው ብለዋል። ከለውጡ በኋላ በምንሰራቸው ስራዎች ሁሉ ስንከተላቸው የነበሩ የፍጥነት፣ የጥራትና የዘላቂነት መርሆዎች የብልጽግናን ጉዞ ውጤታማነት የሚያረጋግጡ ናቸው።

በቀጣይ በዓለም ላይ አሉ ተብለው የሚጠቀሱ ስጋቶች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች፣ ከቴክኖሎጂ ጋር ያሉ አሉታዊ ጉዳዮችና የወረርሽኝ ስጋቶች ናቸው።

https://aapp.gov.et/wp-content/uploads/2022/06/LOGO-w.png

© 2023 Copyright Addis Ababa Prosperity Party

Contact
0116674406
P.O.Box: 1352
303784
Total Visitors